ቱርክ ሩሲያንና ዩክሬንን ለማደራደር ያቀረበችውን ጥያቄ እንደተቀበሏት አስታወቀች

ጥር 17/2014 (ዋልታ) በዩክሬንና ሩሲያ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ቱርክ ያቀረበችው የአደራዳሪነት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታወቀች።
የቱርክ ፍላጎት አሁን የተፈጠረውን ውጥረት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማርገብ መሆኑን የገለፁት የገዥው ፓርቲ (ኤኬ) ቃል አቀባይ ኦማር ሴሊክ አሁን ላይ አንካራ የጥቁር ባህር አካባቢ ሌላ ውጥረት እና ግጭት ውስጥ መግባት የለበትም ብላ እንደምታምን ተናግረዋል።
ሩሲያ ከ100 ሺሕ በላይ ወታደሮቿን ጨምሮ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችና ታንኮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር በማስጠጋት ለወረራ እየተዘጋጀች ነው በሚል አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባዊያን (የኔቶ አባል) አገራት ይከሷታል፡፡
የቱርኩ የዜና ወኪል አናዱሉ ሩሲያ ወታደሮቿ በመደበኛ የልምምድ ተግባር ላይ መሆናቸውንና ዩክሬንና ሌሎች አገራትን ክስ እንደምታጣጥለው አስታውሷል፡፡
ሩሲያ ኔቶ የተስፋፊነት ህልሙን ለማሳካት ዩክሬንን አባል አድርጎ ለማስፈፀም መሞከር እንደሌለበት በመጥቀስ ትሞግታለች፡፡