ቻይና በባይደን ቡድን ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እየጣረች ነው ተባለ

ቻይና በቅርቡ ስልጣናቸውን በሚረከቡት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እየጣረች መሆኑን የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡

በሀገሪቱ ብሔራዊ የደህንነት ተቋም ውስጥ ባልደረባ የሆኑት ዊሊያም ኢቫኒና ቻይና በባይደን ቡድን ውስጥ የሚሰሩ ግለሰቦችን ኢላማ ማድረጓን ገልጸዋል፡፡

በባይደን ቡድን ላይ የተደረገው ተጽዕኖ የተጠናከረ ነበር ያሉት ኢቫኒና፣ በተጨማሪም ቻይና አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማግኘት በምታደርገው ጥረት እና በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ጣልቃ ለመግባት መሞከሯን ነው ያስረዱት፡፡

ኢቫኒቫ ቀጣዩ አስተዳደር ይህንን የቻይና ተፅዕኖ መረዳት መቻል አለበትም ነው ያሉት፡፡

2020 በተደረገው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ትራምፕ ቻይና ባላቸው የባንክ ደብተር እንዲሁም ባይደን ልጃቸው ሃተር ከቻይና ጋር ባካሄደው የንግድ ስምምነት ዙሪያ ስማቸው ሲነሳ እንደነበር አስታውሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡