ቻይና እና ብራዚል የአሜሪካ ዶላር መጠቀምን ለማቆም ወሰኑ

መጋቢት 21/2015 (ዋልታ) በዓለም በኢኮኖሚዋ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ቻይና እና በላቲን አሜሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ብራዚል የአሜሪካ ዶላርን እንደ መገበያያ ላለመጠቀም ተስማሙ፡፡

ሁለቱ አገራት የንግድ ልውውጣቸውን ከዶላር ነጻ በማድረግ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያዬት መወሰናቸው የአሜሪካ ዶላር አቅም እንዲዳከም እና ተፅዕኖም እንዲቀንስ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ቻይና ባለፈው ዓመት በሁለትዮሽ ንግድ ሪከርድ 150 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በማስመዝገብ የብራዚል ትልቋ የንግድ አጋር ሆና እንደነበርም የሲጂቲኤን ዘገባ አስታውሷል፡፡

በተመሳሳይ ኬንያ ከሳውዲ አረቢያ ነዳጅ ለመግዛት የአሜሪካ ዶላር ሳይሆን የኬኒያ ሽልንግ ለመጠቀም መስማማቷ ይታወሳል፡፡