አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

መጋቢት 15/2013 (ዋልታ) – በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ከትካቼንኮ ቬስቨሎድ ጋር በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገለጸ፡፡
አምባሳደር አለማየሁ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ፣ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብ፣ 6ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ሩሲያ እየተጫወተች ላለው ገንብ ሚና አመስግነው፤ ወደፊትም ሩሲያ በመርህ ላይ የተመሰረተ አቋሟን አጠናክራ እንድትቀጥል አምባሳደሩ መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡
በሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ከትካቼንኮ ቬስቨሎድ በበኩላቸው፣ ሩሲያ ለኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት አጠንክራ እንደሚትሰራ በማረጋገጥ፣ ሁለቱም አገሮች የሀሰት መረጃ ስርጭትን በጋራ መከላከል እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡