አራተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እየተካሄደ ነው

ታህሣሥ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) በኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን መካከል አራተኛው ዙር የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ መጀመሩ ተገለጸ፡፡

ይህ የሶስትዮሽ ድርድር እየተካሄደ ያለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ በፈረንጆቹ ሐምሌ 2023 ተገናኝተው የሰጡትን የጋራ መግለጫ መሰረት አድርጎ ነው።

ድርድሩ በህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም ዓመታዊ ስራ ላይ መመሪያዎችን እና ደንቦችን ለማጠናቀቅ የተፋጠነ ድርድር ለመጀመር ያለመ መሆኑ ተተቁሟል።

ከዚህ ድርድር አንድ ቀን ቀደም ብሎ ከሶስቱ አገራት የተውጣጡ ቴክኒካል ባለሙያዎች ስብሰባ አድርገው እንደነበር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡