አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የፀጥታ ፖሊሲ ተወካይ ጋር ተወያዩ

                                                አቶ ደመቀ መኮንን

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የፀጥታ ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦረል ጋር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በስልክ ተወያዩ፡፡

አቶ ደመቀ ክላስተርን መሠረት ባደረገ የማስተባበር ዘዴ እየተተገበረ ባለው የክልሉ የመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ሥራዎች እንዲሁም በክልሉ የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ እየተከናወኑ ያሉት ሥራዎች ላይ ለከፍተኛ ተወካዩ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ሚኒስትሩ በክልሉ ያሉ ሰብዓዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት መንግስት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም ለከፍተኛ ለተወካዩ ገልፀዋል።

                የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የፀጥታ ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦረል

ሁለቱም ወገኖች ባደረጉት ውይይት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረስ ላይ የተጀመሩትን ጥረቶች ለማጠናከር እና በቅርበት መስራታቸውን ለመቀጠል በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት መካከል የጠበቀ ትብብርን ለማጠናከር መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡