የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በታኅሣሥ 16 ቀን 2013 ዓ.ም የቦርዱ አመራሮችና ፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት የመጪው አገር አቀፍ ምርጫን ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ለውይይት እንዳቀረበ ይታወሳል።

በእለቱም ፓለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን ቦርዱም እጩዎችን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ፊርማ የህግ መስፈርት ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ብቻ አገልግሎት ላይ እንዳይውል የተወካዮች ምክር ቤትን መጠየቁ ይታወሳል። በዚሀም መሰረት የመጨረሻው የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ይፋ ሆኗል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም በዚሁ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተግባራቱ አፈጻጸም ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳውቅ ይሆናል።

(ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)