ኢራን ከስምምነት ውጪ ዩራኒየም ልታበለፅግ መሆኑ ተገለፀ

ኢራን ዩራኒየምን በ20 በመቶ ጥራት ለማበልጸግ ማቀዷን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የዓለም አቀፍ ኒውክሌር ስምምነት ጥሰት ሲል ፈርጇል፡፡

የአለም አቀፍ ኒውክለር ስምምነት ኒውክሌር ቦምብ ለመሥራት ከሚፈለገው 90 በመቶ ያነሰ ቢሆንም፤ እ.አ.አ 2015 ላይ የተደረገው ስምምነት ኢራን የምታበለጽገው ዩራኒየም ደረጃ ከ4 በመቶ እንዳይበልጥ ይደነግጋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት የአውቶሚክ ተቆጣጣሪ ክፍል የኢራን ውሳኔ ኒውክሌርን የተመለከተ ዓለም አቀፍ ስምምነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጥስ ነው ብሏል።

ኢራን ስምምነቱን መጣስ የጀመረችው ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ማዕቀቦችን በድጋሚ መጣል በመጀመራቸው ነው።

ዓለም አቀፉ የአውቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (አይኤኢኤ) እንደተናገረው፤ ኢራን በተራራማ አካባቢ በሚገኘው ፎርዶው ፊውል የተባለ የዩራኒየም ማበልጸጊያ ተቋም፤ ዩራንየምን በ20 በመቶ ጥራት የማበልጸግ እንቅድ እንዳላት መረጃ ሰጥታለች ሲል ያስነበበው ቢቢሲ ነው፡፡