ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን የምርጫ ቀኑን ታሪካዊ የዴሞክራሲ ቀን እናደርጋለን – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

                            ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ሰኔ 07/2013 (ዋልታ) –  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን የምርጫ  ቀኑን ታሪካዊ የዴሞክራሲ ቀን እናድርገው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የዛሬ ሳምንት ኢትዮጵያውያን በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ድምፃችንን እንሰጣለን፤ ይህ ምርጫ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሚሆን ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

መላው ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችንን ለማስከበር ወደ ምርጫው በምንሄድበት ወቅት ቀኑን የዜግነት ግዴታችንን በመወጣት የትውልድ ማኅተም ለመተው እንጠቀምበት ነው ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪው ሰኞ ውጡና ድምጽ ስጡ ፤ አረንጓዴ ዐሻራችሁንም አስቀምጡ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው  መልዕክት አስተላልፈዋል።