ኢትዮጵያ ለድርድር የምትቀመጠው ሱዳን ወደነበረችበት ስትመለስ ብቻ ነው – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

 

“ኢትዮጵያ ለድርድር የምትቀመጠው ሱዳን ወደነበረችበት ስትመለስ ብቻ ነው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ መግለጫ የሰጡት አምባሳደር ዲና ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን ሰላማዊ ድርድርን ትመርጣለች ይህንን በተመለከተም ለአለም አቀፍ ማህበረሰቡ እያሳወቀች ነው ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል ፆታዊ ጥቃት፣ ዘረፋ እና ግድያ እየደረሰ ስለመሆኑ ለተነሳላቸው ጥያቄ አምባሳደሩ በትግራይ ክልል በነበረው ፅንፈኛ ቡድን እስረኞች እንድለቀቁ ማድረጉን አስታውሰው፣ ይህን እንደሚያደርጉ ይገመታል፤ ይህም በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ይቀርባል ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልለ መልሶ ማቋቋም እና ሰብዓዊ ድጋፍ በተመለከተ የአለም አቀፍ ተቋማት ፍላጎት እንዳላቸውና ይህንንም መንግስት እንደሚያመቻች የገለጹት አምበሳደሩ፣ በሳምንቱ ውስጥ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሳምንቱ ወደ ኢትዮጵያ ለመጡት የውጭ ሀገር መንግስታት ተወካዮች በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ መግለጫ ተሰጥተዋልም ብለዋል፡፡
(በመስከረም ቸርነት)