ኬኒያ በ2021 6.2 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት እንደምታስመዘግብ አስታወቀች

የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬኒያ በ2020 ከነበረው እድገት ደረጃ 0 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ በማስመዝገብ 6 ነጥብ 2 በመቶ እንደሚያድግ የአገሪቱ ብሄራዊ ግምጃ ቤት አስታወቀ፡፡

ትንበያው ከ2020 ጋር ሲነፃፀር 0 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ እንደሚኖረውም ግምጃ ቤቱ ገልጿል፡፡

በ2020 ሁለተኛውና በሶስተኛው ሩብ አመት የምጣኔ ሃብት መነቃቃት እንደነበርና 5 ነጥብ 7 እድገት መመዝገቡ ተነግሯል፡፡

የ6 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ትንበያን ለማሳካት የተረጋጋ ማይክሮ ኢኮኖሚ ማስፈን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመቆቋም ንግድ ስራ እንቅስቃሴን ማነቃቃት እና በግብርናው ዘርፍ የሚገኘው ምርታማነት ለማሳካት ያግዛል ተብሏል፡፡

እድገቱ ውጤታማ ለማድረግ የገንዘብ ዝውውር ላይ ተንተርሶ የታክስ አሰባሰቡ ላይ በመስራት የታክስ ፖሊሲውና ታክስ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ትልቁን ቦታ ይይዛሉ ተብሏል፡፡

በ2020 የኮቪድ-19 እና የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ኢኮኖሚዋን በምትፈልገው መንገድ እንዳያድግ እንቅፋት የሆነባት ኬኒያ 2 ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎቿ ለስራ አጥነት ተዳርገዋል፡፡