ኢትዮጵያ በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘች

መጋቢት 14/2016 (አዲስ ዋልታ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሞስኮ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አውግዟል፡፡

ሚኒስቴሩ በሽብር ጥቃቱ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሩሲያዊያን እና ለሀገሪቱ መንግሥት መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት እና ህዝብ ጎን እንደምትቆም በመግለጫው አስታውቋል።

በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በሙዚቃ ኮንሰርት አዳራሽ በተፈፀመ የጅምላ ተኩስ በመቶዎች የሚቆጠሩ መገደላቸው እና መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡

ጥቃቱ በሞስኮ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው ኮርከስ ከተማ የተፈፀመ መሆኑን እና ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች አለመታወቃቸው ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሞስኮ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት እንደሚያወግዝ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።