ኢትዮጵያ በፊፋ የሀገራት ደረጃ ስድስት ደረጃዎችን አሻሻለች

መጋቢት 30/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ በዓለም የእግር ኳስ የበላይ ጠባቂ ፊፋ የሀገራት ደረጃ ስድስት ደረጃዎችን አሻሽላለች፡፡
የዓለም እግር ኳስ ማኅበር ፊፋ ባወጣው የሀገራት ደረጃ ኢትዮጵያ ከነበረችበት 146ኛ ስድስት ደረጃዎችን አሻሽላ 140ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
ዋልያዎቹ በቅርቡ ያደረጓቸው መልካም እንቅስቃሴዎች ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ አስችሏቸዋል፡፡ የዓለም እግር ኳስን የቤልጄሙ ወርቃማ ትውልድ በአንደኝነት ይመረዋል፡፡
የ2018 የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ፈረንሳይ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ የዓለም ዋንጫን ብዙ ጊዜ በማንሳት የሚስተካከላት የሌላት ብራዚል ሦስተኛ ደረጃ ላይ ናት፡፡
እንግሊዝ፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን፣ ጣልያን፣ አርጀቲና፣ ዩራጋይና ዴንማርክ በቅደም ተከተል ከአራት እስከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ሳን ማሪኖ 210ኛ የፊፋ የሀገራት ደረጃን በመያዝ በግርጌ ላይ እንደምትገኝ ፊፋ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡