ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የ258.8 ሚሊየን ብር የእርዳት ስምነት ተፈራረሙ

ሐምሌ 2፣ 2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የ258 ነጥብ 83 ሚሊየን ብር የእርዳታ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

እርዳታው ለስራ ፈጠራ በተለይም አነስተኛ እና በሴቶች የሚንቀሳቀሱ የንግድ ስራዎችን ለመደገፍ ያለመ መሆኑን ፡፡

የእርዳታ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህምድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አርቱሮ ሉዚ መፈራረማቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡