እባብ መሳይ ፍጥረት ከነ ሕይወቱ ከሰው ሆድ በቀዶ ጥገና ወጣ

መጋቢት 13/2016 (አዲስ ዋልታ) 30 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው እባብ መሳይ ፍጥረት ከአንድ ሰው ሆድ ውስጥ በቀዶ ጥገና መወገዱ ተሰማ።
በተደጋጋሚ ሆዱን ይቆርጠው በነበረ ሰው ላይ ሐኪሞች ባደረጉት ቀዶ ጥገና እባብ መሳይ ፍጥረት ከነ ሕይወቱ ማውጣት ችለዋል።
በተደጋጋሚ የሆድ ቁርጠት ህመም የሚሰማው አንድ ቬትናማዊ ወደ ሆስፒታል አምርቶ በተደረገለት ምርመራ በሆዱ ውስጥ መጠኑ ባልተለመደ መልኩ ከፍ ያለ ተንቀሳቃሽ አካል መኖሩ ተረጋገጠ።
በዚህም በተደረገለት የቀዶ ህክምና 30 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው እባብ መሳይ ፍጥረት ከሆዱ ውስጥ ወጥቶለታል።
ፍጥረቱ በግለሰቡ መቀመጫ በኩል ገብቶ ሊሆን እንደሚችል በሐኪሞቹ ከተሰጠው ግምት ውጭ እንዴት ይህን ያህል መጠን ያለው ፍጥረት በሆድ ውስጥ መፈጠር እና መቆየት ቻለ ለሚለው ጥያቄ እስካሁን ሳይንሳዊ ምላሽ መስጠት አልተቻለም።
እንደ ኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ እባብ መሳይ ፍጥረቱ የታካሚውን አንጀት ሲጎዳው እንደቆየ ቢገለጽም አሁን ሰውየው በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል ተብሏል።