የቀመሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ ተመለሰ

 

መጋቢት 13/2016 (አዲስ ዋልታ) የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ምርት ሂደት መመለሱን ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ አስታወቁ።

በሰሜኑ ግጭት ምክንያት ላለፉት ግዜያት ስራ አቁሞ የቆየው ፓርኩ ኮርፖሬሽኑ ባዳረገው ከፍተኛ ርብርብና በተሰጠው ትኩረት በዛሬው ዕለት ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ያመርቱ የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እንዲሁም አዳዲስ ኢንቨስተሮች በፓርኩ ለማምረት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎቻቸውን እያጠናቀቁ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ኩባንያዎቹ ወደ ምርት ሂደት እንዲገቡ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል።

ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት እንዲገባና ውጤታማነቱ ከፍ እንዲል እንዲሁም ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ለመፍጠር እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅርበት እንዲደግፉም ዋና ስራ አስፈፃሚው በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ238 ሄክታር መሬት ላይ ተገንብቶ በ2009 ዓ.ም ስራ የጀመረና 15 የማምረቻ ሼዶች እንዲሁም የለማ መሬት ለኢንቨስተሮች ዝግጁ መደረጉ ተጠቁሟል።