ከተማ አስተዳደሩ የ6 ወራት የሥራ የአፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስድስት ወራት የሥራ የአፈጻጸም ግምገማ እየያካሄደ ነው፡፡

በግምገማው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ መለስ አለም እንዲሁም ከ500 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ግምገማው ከስድስት ወር በፊት በእቅድ የተያዙ በከተማዋ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን መነሻ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ግምገማው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ አግልግሎት ሰጭ ተቋማት ተናቦ መስራት መቻል እና ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ መዋቅሮች ተመሳሳይ አሰራር ሂደት መከተልን መሰረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአፈጻጸም ተግባሩ በተለያዩ አካላት የተገመገመ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአዲስ አበባ ምክር ቤት እንዲሁም በፓርቲ ጽ/ቤት ቁጥጥር እና ዳሰሳ ተደርጎበታል፡፡

የአፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ የአገልግሎት ተጠቃሚው ያለውን የእርካታ መጠን እንዲያሳይም ተሞክሯል፡፡

በተጨማሪ በከተማዋ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ የተሰሩ ስራዎችንም የሚመለከት ነው፡፡

አመራሮች እርስ በእርስ ተናበው እና ተግባብተው መስራታቸው በከተማዋ የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖረውም አድርጎታል ተብሏል፡፡
(በመስከረም ቸርነት)