የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 5ሺህ 116 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 5ሺህ 116 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቅድመ እንዲሁም በድህረ ምረቃ መርኃግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ሲሆን፣ ከተመራቂዎቹ መካከል 1ሺህ 623ቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሰቲው ከሚያስመርቃቸው መካከል 9ኙ በዶክትሬት ዲግሪ ሲሆን፣ 40 የሚሆኑ ደግሞ በልዩ ፍላጎት ማስተርስ ዲግሪ ያሰለጠናቸው ናቸው።

(በበኃይሉ ጌታቸው)