ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባን ያስዋቡ ተቋማትና ኩባንያዎችን አመሰገኑ

ጥር 25/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥሪን ተቀብለው ከተማዋን ውብ ላደረጉ ተቋማትና ኩባንያዎች ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቀረቡ፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው 35ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ መነሻ በማድረግ ከተማዋን ላሳመሩ ተቋማትና ኩባንያዎች ነው ምስጋና ያቀረቡት፡፡