የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል እየተከበረ ነው

ጥር 1/2014 (ዋልታ) በደቡብ ክልል የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ (ሴራ) በዓል በቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው።
በዓሉ እየተከበረ ያለው በሲምፖዝየም ሲሆን የብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደር መተዳደሪያ ደንብ የሆነውን ሴራን መሰረት አድርጎ የሚከወን እንደሆነ ተጠቁሟል።
በዘመን መለወጫ በዓሉ ላይ የዞኑና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከየወረዳው የተውጣጡ የብሔረሰቡ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።
የሴራ በዓል በወረዳ ደረጃ በየዓመቱና በዞን ደረጃ ደግሞ በየሁለት ዓመቱ የሚከበር ነው።