ኬንያ የሁሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች ያለቪዛ ወደ አገሯ እንዲገቡ ልትፈቅድ መሆኗን ገለጸች

ጥቅምት 19/2016 (አዲስ ዋልታ) ኬንያ የቪዛ ገደቦችን በማንሳት ሁሉም አፍሪካዊያን ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ወደ ግዛቷ መግባት እንዲችሉ በሯን ለመክፈት መዘጋጀቷን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ገለጹ።

“አሁን የቪዛ ክልከላዎች አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠሩብን መሆኑን የተገነዘብንበት ወቅት ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ ቪዛ ጥያቄን ለማስቀረት የሚያስችለው ሃሳብም በመጪዎቹ ሁለት ወራት ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸዋል።

በአህጉሪቱ አገራት መካከል ከቪዛ ነጻ ጉዞ እንዲኖር ማድረግ ከአፍሪካ ኅብረት ያለፉት ዓመታት ግቦች አንዱ እንደነበርም የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል።

በአውሮፓዊያኑ 2022 በወጣ አንድ ሪፖርት ሲሸልስ፣ ጋምቢያ እና ቤኒን እስካሁን ለአህጉሪቱ ዜጎች ከቪዛ ነጻ ጉዞን መፍቀዳቸው ተመላክቷል።