ኮሚሽኑ የሩብ ዓመት የሥራ እድል ፈጠራ እቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው

ግንቦት 13/2013 (ዋልታ) – የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን የ3ኛው ሩብ አመት የሥራ እድል ፈጠራ እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ የፌደራል እና የክልል አካላት በተገኙበት በጋራ እየገመገመ ይገኛል፡፡

የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ንጉሱ ጥላሁን  ባለፈው አመት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ  ከ300 ሺህ በላይ የስራ እድሎችን ማምከኑን ገልጸው ዘንድሮ በዚህ ዘርፍ ጫና እንዳያሳድር የተሰሩ ስራዎች አመርቂ በመሆናቸው የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

አክለውም በስራ እድል ፈጠራው የሚተገበሩ መመሪያና ፖሊሲዎችን በማሻሻል እና  አዳዲስ ስትራቴጂ በመቅረጽ ወደ ስራ መገባቱንም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2ሚሊየን 812 ሺህ 410 የስራ እድሎች እንደተፈጠሩ ተገልጿል።

ከዚህ ውስጥ 29 በመቶ በግብርና፣ 30 በኢንዱስትሪው እንዲሁም 41 በመቶ በአገልግሎት ዘርፍ የተፈጠሩ ናቸው ተብሏል።

ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም 21 በመቶ እድገት ማሳየቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

(በስመኝ ፈለቀ)