የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጅ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ጉባኤ እያካሄደ ነው

ግንቦት 13/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የጥጥ፣ የጨርቃጨርቅ እና የአልባሳት የእሴት ሰንሰለት በአፍሪካ በሚል ዓለም አቀፍ ጉባኤ እያካሄደ ነው።
በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ዘጠነኛው ጉባኤ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ የፋሽን ሾው የሚቀርብ ይሆናል።
በጉባኤው የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሥራ አስኪያጆች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ባለሀብቶች እና ከኢትዮጵያም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
(ምንጭ፡- አሚኮ)