የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ሰጠ

መጋቢት 13/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል በስራ አፈፃፀማቸው ውጤታማ ለሆኑና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ ከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ሰጥቷል።

ቢሾፍቱ በሚገኘው የአየር ኃይሉ ጠቅላይ መምሪያ በተደረገው ስነ ሥርዓት የማዕረግ እድገቱ ተሰጥቷል።

የማዕረግ እድገት የተሰጣቸው በስራ አፈፃፀማቸው ውጤታማ ለሆኑና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ ከፍተኛ መኮንኖች መሆኑም ተገልጿል።

የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ለከፍተኛ መኮንኖቹ ማዕረጉን ሰጥተዋል።

የማዕረግ እድገት የተሰጣቸው ባለፈው ዓመታት ለተቋሙ ሁለንተናዊ ለውጥ የራሳቸውን አበርክቶ ያደረጉ አባላት እንደሆኑ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።