የመከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት

መስከረም 5/2014 (ዋልታ) ከሐረሪ ክልል በ2ኛ ዙር የመከላከያ ሰራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ዛሬ ሽኝት ተደረገላቸው።
ኢትዮጵያ ላደረገችላችሁ ጥሪ የሰጣችሁት ፈጣን ምላሽ አኩሪ ነው ሲሉ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አብዱጀባር መሀመድ በሽኝቱ ላይ ተናግረዋል፡፡
ሐረር ከራሳቸው አልፈው አገርን የሚወዱ ጀግና ወጣቶችም እንዳላት አስመስክራችኋል ብለዋል፡፡
የሐረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ናስር ዩያ በበኩላቸው ታግሎ ለአገርና ለሕዝብ ህይወትን መስጠትን ያህል አኩሪ ተግባር የለም ማለታቸውን የሐረሪ ብዙኃን መገናኛ ዘግቧል፡፡