የመጀመሪያ ሆነው የሲቪል ማህበረሰብ፣ የግል ድርጅቶችና የመንግስት አጋርነት ኤግዚቢሽን ተከፈተ

የሲቪል ማህበረሰብ፣ የግል ድርጅቶችና የመንግስት አጋርነት ኤግዚቢሽን

መጋቢት 28/2013 (ዋልታ) – የመጀመሪያ ሆነው የሲቪል ማህበረሰብ፣ የግል ድርጅቶችና የመንግስት አጋርነት ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ፡፡

ለሶስት ቀናት የሚቆየው ኤግዚቪሽኑ “የመንግስት የሲቪል ማህበረሰብና የግል ድርጅቶች ትብብር ለጋራ ልማት” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ኤግዚቪሽኑን የከፈቱት የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ ናቸው፡፡

በኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ለውጥ ለማምጣትና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሲቪል ማህበረሰብ፣ የግል ድርጅቶች እና የመንግስት አጋርነት ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡

መንግስት ብቻውን ጠንክሮ ስለሰራ የሚፈለገው ውጤት ስለማይመጣ የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

የሲቪል ማህረሰበ ቀን ኤግዚቪሽን ማክበሩ ዘርፉ ለሃገር ልማት ግንባታ ማበርከት የሚገባውን አንዲያበረክትና ማህበረሰቡ የበጎ አድራጊነት ባህሉን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑም በምክፈቻው ስነ-ሥርዓት ወቅት ተነግሯል፡፡

(በምንይሉ ደስይበሉ)