የተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በዳርፉር የተሰጠውን የሰላም ማስከበር ተግባር አጠናቀቀ

በሱዳን ዳርፉር በእ.አ.አ 2003 የተከሰተውን  ግጭት ተከትሎ  ወደ አካባቢው የገባው   የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልእኮ  ከ13 ዓመታት  አገልግሎት በኋላ በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትላንት ባወጣው መግለጫ የሰላም አስከባሪ ተልእኮው መጠናቀቁን ተከትሎ የሱዳን መንግሥት በክልሉ ለሚገኙ ዜጎች ደህንነት እና አገልግሎት የመስጠት ሓላፊነቱን ይወስዳል ብሏል፡፡

በሥልጣን ላይ ያለው ጊዜያዊ የሱዳን መንግሥትም በዴሞክራሲያዊ  መንገድ ምርጫ  በማድረግ  በዳርፉር ያለውን ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተልእኮው እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 1 ቀን 2021 ጀምሮ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ፣ ለሠራተኞች እና እዚያ ለሚገኙ ንብረቱ  ደህንነት ትኩረት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ቀስ በቀስ ለቅቆ ለመውጣት የስድስት ወራት ጊዜ እንዲሰጠው 15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አጽድቀውታል፡፡

በ2003 በሱዳን ምዕራባዊው ክፍል በመንግሥት ወታደሮች እና በአማፅያን  ቡድኖች መካከል የተቀሰቀሰውን የከፋ ግጭት ለማስቆም በ2007 የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይል  በዳርፉር መሰማራቱ የሚታወስ ነው፡፡

በዳርፉር የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልእኮ ስር በአሁኑ ወቅት ከ7ሺህ 500  በላይ ወታደሮች፣  ፖሊሶች፣ ሲቪል ሠራተኞች በአካባቢው ተሰማርተው  እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

(ምንጭ፡-አልጀዚራ)