የቱርክ ፕሬዝዳንታዊ እና የፓርላማ አባላት ምርጫ እየተካሄደ ነው

ግንቦት 6/2015 (ዋልታ) የቱርክ ፕሬዝዳንታዊ እና የፓርላማ አባላት ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል።

በርካታ ቱርካዊያን ለቀጣይ 5 ዓመታት አገራቸውን የሚመራ ፕሬዝዳንት እና የፓርላማ ተወካዮቻቸውን ለመምረጥ በማለዳ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በማቅናት ድምጽ እየሰጡ እንደሚገኙም ተገልጿል።

በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ሬስፕ ጣይብ ኤርዶሃን እና የስድስት ፓርቲዎችን ድጋፍ ያገኙት ከማል ክሊችዳሮግሉ እንደሚፎካከሩም ተጠቁሟል።

24 ፓርቲዎችና 151 የግል እጩ ተፎካካሪዎች 600 መቀመጫ ባለው የቱርክ ፓርላማ ወንበር ለማግኘት የመራጮችን ድምጽ ይጠባበቃሉም ነው የተባለው።

64 ሚሊየን ቱርካዊያን በምርጫው መሳተፍ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን ከ2 ሚሊየን በላይ ከቱርክ ውጭ የሚገኙ የሀገሪቱ ዜጎችም በያሉበት ድምጻቸውን ሲሰጡ መሰንበታቸውን የቲአርቲ ዘገባ አመላክቷል።