ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት መረጃ ሥርዓትን ጎበኙ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ግንቦት 6/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በልጽጎ ሥራ ላይ የዋለ የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት መረጃ ሥርዓትን ጎበኙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት ሥርዓቱ የዜጎችን የመረጃ አያያዝ ዘመናዊ በማድረግ በዜጎች ላይ ይደርሱ የነበሩ ችግሮችን በማስቀረትና በውጭ ሀገራት ሥራ ሥምሪት ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ የሚኖረው ሚና ጉልሕ ነው።