የቱኒዚያ ኢንቨስተሮች የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ፋብሪካዎችን ጎበኙ

የቱኒዚያ ኢንቨስተሮች

መጋቢት 28/2013 (ዋልታ) – ከቱኒዚያ የመጣ የኢንቨስተሮች ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ እና አካባቢዋ ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እና ፋብሪካዎችን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱም የኢንቨስተሮች ቡድኑ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና በኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ኮርፖሬሽን አማካኝነት እንደ ጨርቃ ጨርቅ፣ ፓርማሲዩቲካል እና አይ ሲ ቲ የመሳስሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን መመልከታቸውን  ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የቱኒዚያ ኢንቨስተሮች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በቅርቡ መዋለንዋያቸውን ያፈሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡