የትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ በወሎ ግንባር

መስከረም 13/2014 (ዋልታ) የትምህርት ሚኒስቴር አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ለመደምሰስ እየተፋለመ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነት ለማሳየት ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የበሬ ሰንጋዎች በወሎ ግንባር ድጋፍ አደረገ፡፡
በሚኒስቴሩ የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ዳይሬክተር የሰውዘር በላይነህ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነት ለማሳየት ድጋፉ መደረጉን ተናግረዋል።
በቀጣይም ለሰራዊቱ የሚያደርጉትን የደጀንነት ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በወሎ ግንባር የኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ ተወካይ ሰራዊቱ አሸባሪውን ኃይል በአጭር ጊዜ ለማጥፋት ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ለሰራዊቱ ያሳየውን ደጀንነት በማመስገን፣ ድጋፉ ጠላትን በአጭር ጊዜ ለማጥፋት ለሰራዊቱ ከፍተኛ የሞራል ስንቅ እንደሆነም ገልጸዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ በበኩላቸው፣ በወሎ ግንባር ጠላትን ለመደምሰስ አኩሪ ጀብድ እየፈጸመ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተደረገው ድጋፍ ድሉን ለማፋጠን ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ለዋልታ ተናግረዋል።
ሳራ ስዩም (ከወሎ ግንባር)
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!