የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍን ማቀላጠፍ ለብሔራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ግንቦት 24/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍን ማቀላጠፍ ለብሔራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ መሆኑን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፋችንን ማቀላጠፍ ለብሔራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ መሆኑን እንገነዘባለን፤ ለዚህም ነው በዚህ ዙሪያ የኢትዮጵያ ብልጽግና ራዕይ ትኩረት እያደረግን ያለነው” ብለዋል።