የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ ነው – መንግሥት

ኅዳር 22/2015 (ዋልታ) የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሰጠው ወቅታዊ መረጃ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ ነው።

በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጀው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከትናንት ኅዳር 21 ቀን ጀምሮ ሽሬ ላይ ሥራውን ጀምሯል።

ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታጣቂዎች የተወጣጣው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሥራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይታመናል።

ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመልስ ይሆናል።

ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ፣ በቴክኒክ ጉዳዮችምክንያትመዘግየቱ ይታወቃል።

ኅዳር 22 ቀን 2015 ዓ/ም

አዲስ አበባ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት