የአልጀሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

ሐምሌ 21/2013(ዋልታ) – የአልጀሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራማታን ላማምራ ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል ፡፡

በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም ሚኒስትሩ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡