የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍ ሠልፍ እያካሄዱ ነው

በጋሞ ዞን የአርባምንጭ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አመራር የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ በመደገፍ ሠላማዊ ሠልፍ እያካሄዱ ነው።

ነዋሪዎቹ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ወደ አርባምንጭ ሁለገብ ስታዲየም በማምራት ላይ ይገኛሉ።

ሠልፈኞቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተሰጠው በሳል አመራር የመጣውን ሀገራዊ ለውጥና የብልጽግና ጉዞ እንደሚደግፉ የሚገልጽ መፈክር እያስተጋቡ ነው።

ብልጽግናን በጋራ ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቅሴ የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውንም  ገልጸዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ነዋሪዎቹ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማደናቀፍ የሚጥሩትን የሚያወግዝ እና  ለግድቡ ግንባታ ስኬታማነት ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን እየገለጹ ነው።