የአንጋፋው ድምፃዊ አየለ ማሞ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ

መጋቢት 30/2013 (ዋልታ) – የአንጋፋው ድምፃዊ ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ አየለ ማሞ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ፡፡
የማንዶሊኑ ንጉስ አርቲስት አየለ ማሞ ከዜማና ግጥም ደራሲነቱ በተጨማሪ ለአንጋፋ ድምጻውያን በርካታ ዜማዎችን ሰርቶ ከመስጠት ባለፈ ወይ ካሊፕሶ በሚለው ሙዚቃ በህዝብ ዘንድ ይበልጥ እውቅናን አግኝቷል፡፡
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ1950ዎቹ ጀምሮ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ አንጋፋ ባለሙያ መሆኑም ይጠቀሳል፡፡
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ዛሬ ቤተሰቦቹ ፣ ዘመድ አዝማዶቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ በተገኙበት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡
ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት በአርቲስቱ እረፍት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡
(በሱራፌል በቀለ)