የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ይጀምራሉ- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

የ2012 ዓ.ም የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እንደሚጀምሩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን የ2012 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ለማስቀጠል ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ መተላለፉ የሚታወስ ነው።

ሆኖም በትግራይ ክልል በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተስተጓጉሎ የነበረ በመሆኑ በድጋሚ ጥሪ ማስተላለፍ ማስፈለጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው በደረሰበት ጉዳት ጥገና ላይ በመሆኑ ቀሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመረቁት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ተገልጿል።