የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መጀመሩ ተገለጸ

የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ገለጸ።

በትግራይ ክልል የአድዋ ከተማ በጥፋት ቡድኑ ጉዳት የደረሰበት የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ አገልገሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

መሠረተ ልማቱን ለመጠገን የፌዴራል መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት አብዛኞቹ የትግራይ አካባቢዎች የመብራት አገልግሎት እንዳገኙ መገለጹ ይታወሳል።

በጁንታው ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአድዋ የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ከተማው የመብራት አገልገሎት ዛሬ አግኝቷል።

የአክሱም፣ ሽሬና ሑመራ ከተሞችም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።