የኢትዮዽያ ወጣቶች ፎረም ተመሰረተ

ግንቦት 27/2013 (ዋልታ) – የኢትዮዽያ ወጣቶች ፎረም አደረጃጀት የሀገርን ሰላምና የአንድነት እሴት እንዳይናድ የሚሰራ አደረጃጀት መሆኑ ሲነሳ ወጣቱ ሀይል ሀገር የመቀየር አቅም ስላለው በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ተብሏል::

የኢትዮጵያ ወጣቶች ፎረም የሀገርን ሰላም የሚያስቀጥል ትውልድ ከመፍጠር አኳያ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል::

ወጣት የሀገር ሀብት በመሆኑ ከ70በመቶ በላይ ወጣት ሀይል ያላት ኢትዮጵያ መሰል የወጣት ፎረሞችን በማስፋፋት ለሰላም እና አንድነት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ተብሏል::

የማህበራዊ ችግሮች አፈታት ብሎም አንድነትን ለማጠናከር የውስጥ ችግርን በጋራ ለመፍታት እና መሰል የሰላም ተግባራትን ለመከወን የስርፀት ስራዎችን በጥናት የተደገፈ ለማድረግ ጅማሮዎች መኖራቸው እንዲሁ ተመላክቷል::

(በሄብሮን ዋልታው)