የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፍቅረኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ አበባ ወደተለያዩ ሀገራት እያጓጓዘ ነው

ጥር 26/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፍቅረኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ አበባ በስፋት ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት እያጓጓዘ ማሆኑን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ለበዓሉ የሚሆን አበባን ከኢኳዶር፣ ኮሎምቢያ፣ ሚያሚ፣ ናይሮቢ እና አዲስ አበባ ወደተለያዩ መዳረሻዎች እያጓጓዘ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

የፍቅረኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የካቲት 7 የሚከበር ሲሆን ቀኑን ምክኒያት በማድረግ የአበባ ሽያጭ በከፍተኛ ደረጃ የሚደራበት ወቅት መሆኑ ይታወቃል፡፡

በተያያዘ መረጃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሩሲያ ሞስኮ የሚያደርገውን በሳምንት የሦስት ጊዜ በረራ ከሰኔ ወር ጀምሮ ወደ አራት ከፍ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል፡፡