የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

መጋቢት 15/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለዲቦራ ፋውንዴሽን የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ።

ድጋፉን ለፋውንዴሽኑ መስራችና ባለቤት አባ ዱላ ገመዳ ያስረከቡት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ናቸው።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ በኢንቨስትመንት ዙሪያ ከሚሰራው ስራ በተጨማሪ ለሀገር ትልቅ አበርክቶ ላላቸው ፕሮጀክቶች ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።

የገንዘብ ድጋፉን የተረከቡት የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት አባ ዱላ ገመዳ በበኩላቸው ድጋፉ ለሌሎች ተቋማት፣ ባለሀብቶችና ለሚመለከታቸው አካላት በመልካም አርአያነት ያገለግላል ብለዋል።

ዲቦራ ፋውንዴሽን በአእምሮ እድገት ውስንነት ላይ የሚሰራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን ዓላማውም የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች ለሀገራቸው የሚጠቅሙ እንዲሆኑና ማህበረሰቡም እንደ ችግር እንዳይመለከተው ማድረግ ነው።

ኮርፖሬሽኑ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ድጋፍ ለሚሹ አካላት የአልባሳትና የቁሳቁስ ፤ የትምህርት መሳሪያዎችና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ሲያበረክት የቆየ ሲሆን በቅርቡም በአዳማ ከተማ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጡ