የኦሮሚያ ልማት ማህበር የተመሰረተበትን 28ኛ አመት እያከበረ ነው

የኦሮሚያ ልማት ማህበር
መጋቢት 21/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) የተመሰረተበት 28ኛ አመት የምስረታ በአል በልደታ ክፍለ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
የኦሮሚያ ልማት ማህበር በክልሉ በመንግስት ሊሸፈኑ ያልቻሉን የመሰረተ ልማት ፍላጎቶች ባለሀብቶችን በማስተባበር ድጋፍ የሚያደርግ ማህበር ነው::
የልደታ ክፍለ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ኃላፊ ስንታየሁ ተረፈ ማህበሩ ከምስረታው ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን ገልጸዋል።
የልደታ ክፍለ ክተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር 3ሺህ 469 አባላት ሲኖሩት፤ አባላቱን እና የተለያዩ ባለሀብቶችን በማስተባበር በያዝነው አመት 2.5 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን እና በክልሉ ላሉ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች እና በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ ማዋሉን ኃላፊው ገልጸዋል።
በክብረ በዓሉ ላይ ከክፍለ ከተማ የተውጣጡ ተሳታፊዎች የሀይማኖት አባቶች እና አባገዳዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
(በሄለን ታደሰ)