የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት በተደረገው ድጋፍ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ብርሀኑ ቡጤ እንዲሁም የኦሮሚያ አርቲስቶች ማህበር ተገኝተዋል::

የመከላከያ ኢንዶክትሬሽን ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም እንዲሁም በኦሮሚያ አርቲስቶች ማህበር ኢትዮዽያን ከጥፋት ቡድኑ ለታደጋት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል::

የሀገር ህልውናን ብሎም ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው መስእዋት ለሆኑ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚደረጉ ድጋፎች አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባም ተገልጿል::

(በሄብሮን ዋልታው)