የከተማ አስተዳደሩ የ2016 በጀት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

ሐምሌ 2/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም በጀት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ፡፡

የከተማዋ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር በጀት በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

ከቀረበው በጀት 23 ቢሊየን 498 ሚሊየን 446 ሺሕ 197 ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 69 ቢሊየን 336 ሚሊየን 835 ሺሕ 72 ብር ለካፒታል ወጪ እንዲሁም ለመጠባበቂያ በጀት 5 ቢሊየን 300 ሚሊየን ብር በጀት እንደተያዘ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም ለክፍለ ከተሞች መደበኛ በጀት ወጪ 33 ቢሊየን 498 ሚሊየን 495 ሺሕ 1 ብር፣ ለካፒታል ወጪ 8 ቢሊየን 657 ሚሊየን 773 ሺሕ 794 ብር መመደቡን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በጥቅሉ ምክር ቤቱ ለአስተዳደሩ የ140 ቢሊየን 291 ሚሊየን 550 ሺሕ 64 ብር በጀት ለመደበኛ፣ ካፒታልና መጠባበቂያ በጀት በማፅደቅ ጉባዔውን እንዳጠናቀቀ ተጠቁሟል፡፡