የኮቪድ-19 ክትባት በመቐሌ መሰጠት ተጀመረ

መጋቢት 4/2013 (ዋልታ) – የኮቪድ-19 ክትባት በመቐሌ ከተማ መሰጠት ተጀምሯል፡፡

መርሐ ግብሩን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በመቐሌ አጠቃላይ ሆስፒታል አስጀምረውታል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋና የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላትም ተከትበዋል።

የኢዜአ ዘገባ እንዳመለከተው ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎችና ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ለ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች የሚሆን ክትባት ማግኘቷ ይታወቃል።