ዩኤስኤይድ በትግራይ ክልል ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የ181 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ሰኔ 03/2013 (ዋልታ) – የአሜሪካ አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) በትግራይ ክልል ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚውል የ181 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የተደረገው ድጋፍ በክልሉ አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሶስት ሚሊየን ዜጎች የሚውል 100 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ ለማድረስ ያስችላል ተብሏል፡፡

ይህም የምግብ፣ የንጹህ መጠጥ፣ መጠለያ፣ የጤና አገልግሎትን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡

በአሜሪካ መንግስት በኩል እንደ አዲስ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ከዚህ በፊት ከተደረገው 305 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡