ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኦሮሚያ ክልል ከሁሉም ዞኖች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

የካቲት 14/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኦሮሚያ ክልል ከሁሉም ዞኖች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ዛሬ ጠዋት ከኦሮሚያ ክልል ከሁሉም ዞኖች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል ብለዋል።

የዛሬው ስብሰባም በክልሉ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቅርቡ ከተደረጉ ውይይቶች የቀጠለ መሆኑን አስታውቀዋል።