ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ

ሐምሌ 13/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከፕሬዚዳንቱ ጋር በሁለትዮሽ እና በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል፡፡

እንዲሁም በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ሰላም ማምጣት በሚቻልበት መንገድ ላይ በስልክ መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል፡፡