ጠ/ሚ ዐቢይ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ምስጋና አቀረቡ

የካቲት 25/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዴቪድ ቢስሊ ምስጋና አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዋና ሥራ አስፈጻሚው በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት አስመልክቶ ላደረጉት ገንቢ አስተዋጽኦ እና ተጨባጭ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የሚያከናውነው ሥራ የሚደነቅ እና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው የሚታወስ ነው፡፡