ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አስመራ ገቡ

መጋቢት 16/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ከሰዓት አስመራ መግባታቸውን ከኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስመራ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡